አገልግሎቱ በገዜ ጎፋ ወረዳ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የ2 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ - ብሔራዊ መረጃ ማዕከል
አገልግሎቱ በገዜ ጎፋ ወረዳ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የ2 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የ2 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
የአገልግሎቱ ምክትል ጀነራል ዳይሬክተር ርስቱ ይርዳ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች በሥፍራው ተገኝተው አጽናንተዋል፡፡
የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የሁለት ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።
በአካባቢው ስጋት ያለባቸው ዜጎች መንግስት በሚያመቻቸው አማራጭ ከስጋት ቀጣናው እንዲወጡ ለማድረግ በትብብር እንደሚሰራም ገልጸዋል፡፡
አገልግሎቱ በቀጣይ ለተጎጂዎች የሚያደርገውን ሰብዓዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ርዕቱ ይርዳው መናገራቸውን መረጃው ያመለክታል። ( ፋና)